ወደ ደቡብ አፍሪካ በጀልባ በመጓዝ ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ አደጋ ደረሰ

በትላንትናው ዕለት አስራ ሶስት ስደተኞችን ጭና ወደ ደቡብ አፍሪካ በመጓዝ ላይ የነበረች ጀልባ ላይ በደረሰ የመገልበጥ አደጋ በጀልባዋ ተሳፍረው የነበሩ 7 ኢትዮጵያውያን ህይወት ማለፉን የኬኒያው ዴይሊ ኔሽን ዘገቧል ።

ከታንዛንያ ድንበር ‘ታንጋ’ ግዛት ተነስተው ወደ ደቡብ አፍሪካ በመጓዝ ላይ ከነበሩት 13 ሰዎች መካከል አስራ ሁለቱ ኢትዮጵያውያን እንደነበሩና የጀልባዋ ካፒቴን አስክሬን ባለመገኘቱ ዜግነቱን ማወቅ እንዳልተቻለ የታንዛኒያ ፖሊስ ኮማንደር ‘ኤድዋርድ ቡኮምቤ’ ገልፀዋል ።

በአደጋው ሰባት ሰዎች ሲሞቱ አምስት ሰዎች መትረፍ የቻሉ መሆናቸውን የገለፁት ኮማንደሩ የአንድ ሰው አስክሬን በፍለጋ ላይ መሆኑን ያስታወቁ ሲሆን በሟቾቹ የቀብር ሁኔታ ዙሪያም ከታንዛኒያ የኢትዮጲያ ኤምባሲ ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል ።

ምንጭ: ዴይሊ ኔሽን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *