ሳዑዲ ዓረቢያ የመጀመሪያውን የኒውክሌር ማበልፀጊያ ማዕከል ግንባታ አስጀመረች

የሳዑዲ ዓረቢያው አልጋ ወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን ሀገሪቱ የኒውክሌር ባለቤት እንድትሆን የሚያስችላትንና የመጀመሪያውን የኒውክሌር ማበልፀጊያ ማዕከል ግንባታ ስራ አስጀመረ።

ቢን ሰልማን በትናንትናው ዕለት ሰባት የሚሆኑ ፕሮጀክቶችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ከተማ በሆነችው በንጉስ አብዳላዚዝ መርቀው ከፍተዋል።

ፕሮጀክቶቹም የታዳሽ ሀይል፣ የአቶሚክ ሀይል፣ የውሃ ጫዋማነት የሚቀንስ፣ የአውሮፕላን ኢንዱስትሪ እና የዘረመል ህክምና መስጫ ማዕከላት መሆናቸው ታውቋል።

የኒውክሌር ማበልፀጊያ ማዕከሉና የአውሮፕላን ኢንዱስትሪ ትልቅ ትኩረት የሚሰጣቸው ፕሮጀክቶች እንደሆኑ ተጠቁሟል።

በመጋቢት ወር ልዑሉ ኢራን ከያዘችው አቋም በመነሳት ሳዑዲ አረቢያ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ለመታጠቅ መዘጋጀቷን መናገሩ ይታወሳል።

በወቅቱ ቢን ሰልማን ከ ‘CBS’ ከተሰኘ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቆይታ ሳዑዲ ዓረቢያ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ የማበልፀግ ፍላጎት እንደሌላት የገለፁ ቢሆንም ኢራን መሳሪያውን ከታጠቀች ሀገራቸው መሳሪያውን መታጠቋ እንደማይቀር ገልፆዎ ነበር።

ምንጭ፥ አልጀዚራ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *