በ ጠ/ሚ አብይ አህመድ የተቋቋመው ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ስለቀጣይ ሂደቶች ማብራሪያ አቀረበ

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ፣ የአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዝደንት ከስራ መታገዳቸው ለተጀመረው የእርቅና የሰላም ጉዞ የማይበጅ መሆኑን ተናገረ፡፡

ኮሚቴው ዛሬ አጠቃላይ የስራ አፈፃፀሙን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

መግለጫውም ልዩ ልዩ ንዑሳን ኮሚቴዎችን ማቋቋሙንና ሀላፊነት መስጠቱን ተናግሯል፡፡

ወቅታዊ ችግሮችንና ቀውሶችን ለመፍታት በቂ ጥረት አድርጌያለሁ ብሏል፡፡

ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ከሚገኙ የአለም ሙስሊም ማህበረሰቦች ጋር የልምድ ልውውጥ ማድረጉን ተናግሯል፡፡

ኮሚቴው በአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዝዳንት በሼህ መሀመድ ሸሪፍ ላይ የተደረገው የስራ እገዳ ከወቅቱ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ያልተዛመደና አንድን ግለሰብ ነጥሎ ተጠያቂ ያደረገ ነው፤ ስለሆነም ለጀመርነው የእርቅና የሰላም ጉዞ የማይበጅ መሆኑን ተገንዝበው የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትና የፌዴራል እስልምና ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ሂደቱን በጥሞና እንዲያስቡበት መክሯል፡፡

የጋራ ኮሚቴው የኢትዮጵያን ሙስሊሞችን ሁሉ ያለ ልዩነት የሚያሳትፍና የጋራ የሆነ መጅሊስን ለማዋቀር ውጥን መያዙን ተናግሯል፡፡

ምንጭ፥ ሸገር ራዲዮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *