‹‹ለውጡን የጀመርነው የግድ አስፈላጊ ስለሆነ ነው፡፡»

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በአፍሪካ ኅብረት ልዩ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ሁሉን አቀፍ ለውጥና ማሻሻያዎች ማካሄድ ያስፈለገው ማሻሻያን ለመጀመር ሳይሆን የግድ አስፈላጊ ስለሆነ ነው ብለዋል።

የፓን አፍሪካን ራዕይን በማስታወስ የአፍሪካ መሪዎች የተለዋዋጩ ሉላዊ ዘመንን ፈተናዎች ለመቋቋም ከተናጠል እንቅስቃሴ ይልቅ በጋራ እንዲሰለፉ ጠይቀዋል።

የአፍሪካ መሪዎች ትክክለኛ ተስፋዎችንና እና የለውጥ ግስጋሴ ማዕቀፍ ማስቀመጥ እንደሚጠበቅባቸው በአጽንኦት አሳስበዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በኢኮኖሚ ትብብርና ትስስር አማካኝነት የሚኖር ኅብረት አስፈላጊነትን በንግግራቸው ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ያለውን ተሀድሶ የፖለቲካ ምህዳር መስፋቱን፤ የእስረኞች መፈታትን ፤ በመገናኛ ብዙኃንና የጡመራ ድሮች ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ መነሳቱን ከምንም በላይ ደግሞ ሙስናን በጠንካራ የፍትህ ሥርዓት ለመዋጋት እየተወሰደ ያለውን እርምጃ ዘርዝረዋል።

ዶክተር ዐብይ የጦርነት ትርክትን ወደ ጋራ ትብብር ትርክት በመቀየር ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ያላት ጠንካራ ግንኙነት እንዴት ለአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት አስተዋጽኦ እንዳበረከተ የመንግሥታቸውን ልምድ አካፍለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ለእሳቸው እጅግ አስፈላጊ የሆነውና የመንግሥታቸውም ቁልፍ የለውጥ አካል የሆነው የሴቶች ወደ ውሳኔ ሰጪነት ቁልፍ የአመራር ቦታ መምጣት እና እኩል ተሳታፊነት መሆኑን በድጋሚ አስገንዝበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *